WKW

ፈጣኑ ፈረስ

  • Sale
  • $5.50
  • Regular price $6.99


ፀሀፊ፦ ብሩክታዊት ጥጋቡ (የሮሌክስ ወጣት ሎሬት) እና አሚና አብደላ

አርታኢ፦ ጌታቸው እንዳላማው (ረዳት ፕሮፌሰር) አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ

ዲዛይነር፦ እዮብ አበራ 

"ፀሀይ መማር ትወዳለች" የልጆችን የንባብ ፍቅርና ክህሎት ለማሳደግ በማሰብ ልጆች የአማርኛ ፊደላትን በቀላሉ የሚያውቁባቸውንና መልካም ስነምግባርን የሚያዳብሩባቸውን 32 መጻሕፍት ይዞ ቀርቧል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት 32ቱን ዋናዋና የአማርኛ ፊደላትና ቤተሰባቸውን መሰረት ያደረጉ ሲሆን፣ ይህ “ፈ - ፈጣኑ ፈረስ” ከእነዚህ ተከታታይ መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ይህ በአይነቱና በአቀራረቡ ለየት ያለ መጽሐፍ ፤ ህፃናቱን በሚስብ ታሪክ እያዋዛ ፊደላቱን ቶሎ እንዲለዩና የቃላት ክምችታቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳል፡፡ መጽሐፉን ከማንበብዎ በፊት፣ በሚያነቡበት ሰዓትና ካነበቡ በሁዋላ ከልጆች ጋር የሚሰሩና የልጆችን የማንበብ ክህሎት እንዲፋጠን የሚረዱ አጋዥ መልመጃዎች ተካትተዋል፡፡ ይህንና ተከታታዮቹን መጻሕፍት በመሰብሰብ በፍቅር፣ በጨዋታ እና በትዕግስት እየደጋገሙ ለልጆች በክፍል ውስጥ፣ ከመኝታ በፊት እንዲሁም በማንኛውም በሚያመች ሰዓት ያንብቡላቸው፡፡ አላማችን ማንበብ የሚችሉ ብቻ ሳይሆን፣ ማንበብን የሚያፈቅሩ ልጆች ማፍራት ነው፡፡People who bought this product, also bought