ፀሀፊ፦ ብሩክታዊት ጥጋቡ (የሮሌክስ ወጣት ሎሬት) እና ህይወት ወልዴ
አርታኢ፦ ጌታቸው እንዳላማው(ረዳት ፕሮፌሰር)አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ
ስዕል፦ አስራት ኡርጌሳ
ዲዛይነር፦ እዮብ አበራ
"ፀሀይ መማር ትወዳለች" የልጆችን የንባብ ፍቅርና ክህሎት ለማሳደግ በማሰብ ልጆች የአማርኛ ፊደላትን በቀላሉ የሚያውቁባቸውንናና መልካም ስነምግባርን የሚያዳብሩባቸውን 32 መጻሕፍት ይዞ ቀርቧል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት 32ቱን ዋና ዋና የአማርኛ ፊደላትና ቤተሰባቸውን መሰረት ያደረጉ ሲሆን፣ ይህ “አ - አንበሶቹና አጋዘንዋ” ከእነዚህ ተከታታይ መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ይህ በአይነቱና በአቀራረቡ ለየት ያለ መጽሐፍ ፤ ህፃናቱን በሚስብ ታሪክ እያዋዛ ፊደላቱን ቶሎ እንዲለዩና የቃላት ክምችታቸውን እንዲሳድጉ ይረዳል፡፡መጽሐፉን ከማንበብዎ በፊት፣ በሚያነቡበት ሰዓትና ካነበቡ በሁዋላ ከልጆች ጋር የሚሰሩና የልጆችን የማንበብ ክህሎት እንዲፋጠን የሚረዱ አጋዥ መልመጃዎች ተካትተዋል፡፡ ይህንና ተከታታዮቹን መጻሕፍት በመሰብሰብ በፍቅር፣ በጨዋታ፤ እና በትዕግስት እየደጋገሙ ለልጆች በክፍል ውስጥ፣ ከመኝታ በፊት እንዲሁም በማንኛውም በሚያመች ሰዓት ያንብቡላቸው፡፡ አላማችን ማንበብ የሚችሉ ብቻ ሳይሆን፣ ማንበብን የሚያፈቅሩ ልጆች ማፍራት ነው፡፡